Friday, October 29, 2021

That is why we call the PP government The Ortho-Amhara government.

ልብ በል ወገን አዲስ ድምፅ በተከታታይ ጠቅላዩ ጦርነቱን የሞት የሽረት ጉዳይ አድርገው እንዲሰሩበት እና ከእየ ክልሉ መሪዎች በተጨማሪም ከፋኖ፤ ከልዩ ሃይል እና ከመከላከያ መሪወች ጋር በጋራ በአንድ መድረክ እየቀረቡ ሁላችንንም እንዲያስተባብሩ ስንለምናቸው ከርመናል ፡ዛሬ  በከፊልም ቢሆን  ይህንኑ ለማድረግ ባህርዳር መግባታቸውን ሰምተናል ፡እንግዲህ ጦርነቱን በሚመጥነው መንገድ ብቸኛ ስራቸው አርገው ጊዜ እና እድል የሰጣቸውን የእምየን ወንበር በክብሩ ልክ አገር ለማዳን ሊጠቀሙበት ግድ ይላቸዋል፡፡
ምንም እንኳን በርካታ የጦር አዋቂወች እንዳሉን ብንጠረጥርም ፡ ህውሃት ጥይትም ምግብም ነዳጅም ከትግራ ማመላለስ እንዳለባት የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡ ከትግራይ ወደ አማራ ክልል የሚያስገቡት መንገዶች ደግሞ የህውሃት የደም ስር መሆናቸው የታወቀ ነው፡እነዚህ መንገዶች ዘርፈው የሚወስዱባቸው እና በተለይ ለመግደል ሃይል የሚያመላልሱባቸው መንገዶች ብቻ ሳይሆኑ አጋሮቻቸውም ናቸው ፡እና የመጀመሪያው ስራ መውጫ መግቢያውን አየር ሃይላችን ቢቆጣጠረው መልካም ነው።
ከስድስት ሚሊወን የወጣ ሃይልን መሮቶ የሚያሸንፍ መሪ ካለ ከመቶ አስራ አራት ሚሊወን የሚወጣን ሃይል የሚመራ መሪ ከተሸነፈ መሪ አልነበረም ማለት ነው። ህውሃት በፍፁም ከአቅማችን በላይ  ሊሆን አይችልም  ፡፡አበበ በለው