Tuesday, August 21, 2012

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌደሬሽን ምክርቤት



የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ የዜና እረፍት ስንሰማ መሪርና ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል፣
ክቡር  ጠቅላይ ሚኒስቴር  መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችና ፣ የሃይማኖት እኩልነት፣ በመቻቻልና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ አንድነት እንዲሰፍንና ስር እንዲሰድ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፍፁም ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ በማድረግ በአጠቃላይ ሕገ-መንግሥታዊና ፌዴራላዊ ስርዓቱ ስር እንዲሰድና እንዲከበር ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ ታላቅ መሪ ነበሩ
አገራችን ከነበረችበት ድህነትና ኋላ ቀርነት የሚያላቅቅ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በማመንጨት፤ በማፍለቅና በመተግበር ፤  ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንድታስመዘግብ ከልማቱ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩል  ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በታማኝነት አገራቸውን  አገልግለው ከፍተኛ የለውጥ ተስፋ ያሳዩን  መሪ ነበሩ  ።
አገራችን  ታላቅ መሪዋን ማጣቷ ከፍተኛ ጉዳት ቢሆንም ኢትዮጵያውያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ከመቸውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዕጅ ለእጅ ተያይዘን  የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን  የህዳሴ ጉዞና ራዕይ ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ አገራዊ   የአንድነትና መንፈስ እንደምንረባረብ ቃል እየገባን 
 ለመላ የአገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው       መፅናናትን  እንመኛለን ።

No comments:

Post a Comment