Friday, June 10, 2022







ኦነግ ለኦሮሞ ህዝብ ምኑ ነው?
----
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
----
ከትናንት ወዲያ ከኦሮሞ ድርጅቶች አካባቢ ባንዲራን አስመልክቶ የተጻፈ አንድ ደብዳቤ በኢንተርኔት ላይ መጠነኛ ግርግር ማስነሳቱ ይታወሳል። የኦሮሞዎችን በጎ የማይመኙ የሸይጣን ቁራጮች ያ ግርግር ተስፋፍቶ እርስ በእርስ የምንባላ መስሎአቸው እንደ ጥንብ አንሳ ሬሳችንን ዘነጣጥለው ሊበሉ አስፍስፈው ሲጠብቁ ነበር። ይሁንና ከህዝባችን የወረስነውን የMangudummaa እና የDubbii Qabbaneessuu ስልቶች ተጠቅመን ልዩነታችንን በቀላሉ ፈትተናል። 
-----
እነዚህ ከይሲዎች በተለይ "ኦነግ" የሚለው ስም ሲነሳ እንደ እግር እሳት ያሳምማቸዋል። ይህንን አንጋፋ ድርጅታችንን ስም ለማጥፋት የማያደርጉት ጥረት የለም። ይሁን እንጂ ኦነግን ከኦሮሞ ህዝብ ትግል ማፋታት ከንቱ ድካም ነው። 

በእርግጥ እንላችኋለን። የኦሮሞ ድርጅቶች ሁሉ ለህዝባቸው ነፃነት፣ አንድነት፣ ህልውና እና ክብር ያደረጉት ትግል ሲመዘን የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው። ይህም ከመሠረታዊ ነገር ነው የሚጀምረው።

# ጨቋኝ ስርዓቶች የኦሮሞ ህዝብን ማንነት ለማጥፋት ዘማቻ የጀመሩት ህዝቡ የሚጠራበትን ትክክለኛ ስም በመቀየር ነበር። ገዥዎች "ኦሮሞ" የሚለውን ስም አጥፍተው አፀያፊ ፍቺዎች የሰጡትን ስም በግዴታ በህዝቡ ላይ ጭነው ነበር። ይህንን ሆን ተብሎ የኦሮሞ ህዝብን ለማዋረድ የተደረገውን ሴራ ተዋግቶ ህዝቡ በዓለም ዙሪያ "ኦሮሞ" በተሰኘው ትክክለኛ ስሙ ብቻ እንዲታወቅ ያደረገው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው።

# በታሪክ ሂደት ተበታትነው ወደ መረሳሳት ደረጃ ደርሰው የነበሩትን የምስራቅ፣ የምዕራብ፣ የሰሜንና የደቡብ ኦሮሞዎችን ሙሉእ በሆነ ሁኔታ አንድ ላይ ያሰባሰበው ድርጅት ኦነግ ነው። አሁን ያለው የኦሮሞ ህዝብ አንድነት በአብዛኛው የኦነግ የስራ ውጤት ነው።

# የኦሮሞ ህዝብ በባህሉ፣ በቋንቋው፣ በትውፊቱና በታሪኩ ሳያፍር ማንነቱን እንዲገልጽና ኦሮሞነቱን በየትኛውም መስክ እንዲያሳውቅ ከማንም በላይ የጣረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው። 

# ኦነግ የኦሮሞ ብሄርተኝነት አባት ነው። Orommumaa እና Sabboonummaa የሚባሉትን ጽንሰ ሐሳቦች በመቅረጽ የኦሮሞ ብሄርተኝነትን ያበለፀገው ኦነግ ነው። ከሰላሳ ዓመታት በፊት ኢብሳ፣ ቶላ፣ መገርሳ በሚሉ ስሞች ልጆቹን መጥራቱን አቁሞ የነበረው ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ ኦሮሞ ዛሬ ኮራ ብሎ "ሃዊ፣ ቀነኒ፣ ፊራኦል፣ ኦብሰን፣ ሳርቱ" የሚሉ ስሞችን ለልጆቹ እየሰጠ ያለው ኦነግ በቀየሰው መንገድ inspire ስለሆነ ነው።

# ኦነግ "የቁቤ አፋን ኦሮሞ" አባት ነው። አፋን ኦሮሞ በላቲን ፊደል እንዲጻፍ ምርምር አድርገው ውጤቱን ይፋ ያደረጉት ሼኽ ሙሐመድ ረሻድ እና ኃይሌ ፊዳ ናቸው። እነርሱ ያጠናቀሯቸውን ጥናቶች በማዳበር ለመጀመሪያ ጊዜ በስራ ላይ ያዋለው ግን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው። ኦነግ በሽግግሩ ዘመን ከሰራቸው ስራዎች መካከል ትልቁ አፋን ኦሮሞ የትምህርት ቋንቋ ሆኖ የኦሮሞ ልጆች በቋንቋቸው እንዲማሩ ማድረጉ ነው (በዚህ ረገድ የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኢብሳ ጉተማ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል)። 

# ኦነግ የዘመናዊው የአፋን ኦሮሞ ስነ ጽሑፍ አባትም ነው። በቁቤ አፋን ኦሮሞ የተጻፉ የግጥም እና የልብ ወለድ መጻሕፍትን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳተመው ኦነግ ነው። በቁቤ የሚዘጋጁ ጋዜጦችና መጽሔቶችንም ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳተመው ኦነግ ነው።

# አሁን የስራ ቋንቋ ሆኖ የሚያገለግለውን የተማከለ የአፋን ኦሮሞ ዘይቤንም የፈጠረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው። ለቢሮክራሲ ስራ የሚያስፈልጉና በሂደት ለመጥፋት ተቃርበው የነበሩ የኦሮምኛ ቃላትን ከልዩ ልዩ የኦሮሚያ ዞኖች አሰባስቦ በመዝገበ ቃላት በመሰነድ በመላው ዓለም በሚኖሩ ኦሮሞዎች ዘንድ እንዲታወቁ ያደረገው ኦነግ ነው። 

# ኦነግ የዘመናዊው የኦሮሞ የታሪክ ጽሑፍ አባትም ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በመላው የኦሮሚያ ዞኖች ላይ ያተኮረ የታሪክ መጽሐፍ አሳትሞ ያቀረበው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው (ከዚያ በፊት ይወጡ የነበሩት የታሪክ መጻሕፍት በአንዱ የኦሮሚያ ዞን፣ ወይንም በአንድ የኦሮሞ ነገድ ላይ ብቻ ያተኮሩ ነበሩ)።

# ለመጀመሪያ ጊዜ የገዳ ስርዓትን አተገባበር በተሟላ ሁኔታ የሚተርክ መጽሐፍ የጻፉት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ናቸው። የገዳ ስርዓትን በዓለም ዙሪያ በስፋት ያስተዋወቁት ግን በውጭ ሀገራት የነበሩት የኦነግ የውጭ ግንኙነት ቢሮዎች ናቸው። 

# ኦነግ ሁሉን አቀፍ የኦሮሞ ጥናት አባትም ነው። በኦሮሞ ህዝብ ባህል፣ ታሪክ፣ ኢኮኖሚ፣ ቋንቋና የነፃነት ትግል ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበትን ዓለም አቀፍ ኮንፈረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የኦነግ የውጭ ግንኙነት ቢሮ ነው። በዛሬው ዘመን በዚህ ዘርፍ ተጠቃሽ ሆኖ የወጣው የኦሮሞ ጥናት ማህበር (Oromo Studies Association) የተመሠረተው ኦነግ ሲያዘጋጃቸው በነበሩት ኮንፈረንሶች ላይ ሲገናኙ በነበሩት ምሁራን አማካኝነት ነው።
-----
ኦነግ በነፃነት ትግሉ ዘርፍ ያደረገው አስተዋጽኦ ሲገመገም ደግሞ ከላይ ከሰፈረው በእጅጉ ይበልጣል። ስለዚህ ወደ ዝርዝሩ መግባቱ ለጊዜው አያስፈልገንም። በአጭሩ ግን "ኦሮሞዎች በነገድ፣ በጎሳ፣ በክፍለ ሀገርና በሃይማኖት ሳይለያዩ በኦሮሙማ መንፈስ አንድ ላይ ሆነው በተደራጀ ሁኔታ ለነፃነታቸው እንዲታገሉ የቀሰቀሰ፣ ለትግሉ ያሰማራ እና ያታገለ፣ በዚህም ከኦሮሞ ህዝብ መጠነ ሰፊ ድጋፍ፣ ከበሬታ እና አመኔታ የተሰጠው ዋነኛው ድርጅት ነው" በማለት ማስቀመጥ ይቻላል። የኦሮሞ ህዝብ የትግል መንፈስ ሳይቀዘቅዝ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ የደረሰው ኦነግ ባቀጣጠለው ጎዳና ላይ በመራመድ ነው።
----
ይህ ሲባል ግን ግንባሩ ችግር አልነበረበትም ማለት አይደለም። የግንባሩን እንቅስቃሴዎች ሰንገው የያዙ በርካታ ችግሮች ተፈጥረውበታል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ "ኦነግ በኦሮሞ ህዝብ ትግል ውስጥ አንድም አስተዋጽኦ የለውም" የሚሉት ወጀላቴዎች የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ እያስገረመኝ ነው። 

ከነዚህ ወጀላቴዎች ጋር ቃላት መመላለስ አያስፈልግም። ለጊዜው አንድ ነገር ብቻ ልወርውርባቸው። ኦነግ የሚባል ድርጅት ባይኖር ኖሮ ኦህዴድ የሚባል ድርጅት ባልተፈጠረ ነበር። ኦነግ ባይኖር ኖሮ ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶችም ባልተፈጠሩ ነበር። ኦነግ ባይኖር ኖሮ በዛሬው እለት በልጽግና ብብት ላይ ተሰባስበው የተጣረሰ ጽሑፍ የሚጽፉት ቀለብተኞች ቱሪናፋቸውን አይነፉብንም ነበር። 
-----
ወደዚህ ደግሞ "ኦነግ 40 ዓመት ታግሎ ለኦሮሞ ህዝብ ምንም አልሰራም" የሚሉ አሉ። በእርግጥም ኦነግ በመሳሪያ ተዋግቶ የአራት ኪሎ ቤተ መንግስትን መቆጣጠር አልቻለም። ይህም የራሱ ምክንያት ስላለው ወደ ዝርዝሩ አልገባም። የዕድሜው ጉዳይ ለሚያስጨንቃቸው ሰዎች ግን "የፍልስጥኤም፣ የኩርድ፣ የቺቺኒያ እና የሌሎች ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ብዙ ዓመት ተዋግተው መቼ አሸነፉ?" እንላቸዋለን።
ከዚህ በተረፈ ኦነግ ብዙ ነገር ሰርቷል።
----
ወያኔ በነዛው የበደኖ ፕሮፓጋንዳ ላይ ግግም ብለው የኦነግን አራጅነት ሊያስረዱን ለሚፈልጉት ደግሞ "ዓላማችሁ ኦነግን መምታት ሳይሆን ኦሮሞን መጥላት ነው" ብለን እቅጩን እንነግራቸዋለን (የበደኖውን ፊልም ቀርጾ በቲቪ ያሳየው ወያኔ ነው። ኦነግ ሲያርድ ቀራጩ አጠገቡ ነበረ ማለት ነው? ይገርማል እኮ ጃል)።
----
በመጨረሻም:

No comments:

Post a Comment