Thursday, December 1, 2022

ኦሮሞነቴን ያላከበረች ኢትዮጵያ ፈጽሞ ህልም ናት።


"እኛ ኦሮሞዎች በአማርኛ ቋንቋ በመናገር ተባርከናል።  እኛ ግን የአፍ መፍቻ ቋንቋችንን አፋን ኦሮሞን ለማዳከም የሚደረገውን ማንኛውንም ሙከራ እንከላከላለን።  ይህ መልእክት ለአንዳርጋቸው እና ለመንጋው የተላለፈ ነው።"
************
አንዳርጋቸው ጽጌ "ኦሮሞ በላቲን የሚጠቀምበት ፊደል በግእዝ ሊሆን ይገባል" ያለው ቅ*ር*ሻ*ት ይህንን እውነታ አስታወሰኝ።

"ለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል የኦሮሞን ማንነት ማጥፋት."
ይህን ከላይ ያለውን ሀሳብ ለአጼ ሀይለስላሴ ያቀረበው በ1933 ከቤልጅየም አገር በማህበራዊ ሳይንስ በሁለተኛ ድግሪ ተመርቆ የመጣው አቶ ተድላ ኃይሌ ከውጪ ሀገር ትምህርቱ መልስ የትምህርቱ ዋና ጭብጥ አድርጎ ለኃይለስላሴ መንግስት ያቀረበው ምክረ ሀሳብ ነው።
.
አቶ ተድላ ኃይሌ በዘመኑ የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩ በአቶ ሳህሌ ፀዳሉ እንዲሁም በጠቅላይ ሚንስትሩ አክሊሉ ሀብተወልድ በኩል ዓላማውን በስራ ላይ ለማዋል ተጠቅመዋል።
.
ምን ነበር ዓላማው?
ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ "Pioneer of change in Ethiopia." በሚለው መጽሀፋቸው እንዳስቀመጡት እንደወረደ ተቀራራቢ ትርጉሙ እነሆ:-
"የኢትዮጵያ ነገስታት ኦሮሞዎችን በተመለከተ ሶስት ዓማራጮች አሏቸው:- 

1ኛ ሁሉንም ኦሮሞ ሀብት አልባ ባሮች ማድረግ
2ኛ ኦሮሞን ወደ አማራነት በመቀየር (Assimilation) ማንነቱን ማጥፋት
3ኛ እኛ በምንመድበውና ለእኛ ዓላማ የሚሰሩ ኦሮሞዎችን መርጠን በመሾም በእጅ አዙር እናስተዳድራቸው የሚል ሲሆን አንደኛውንና ሶስተኛውን አማራጮች መጠቀም ለአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ጠቃሚ ቢሆንም በእኛ ሁኔታ ጠቃሚ አይደለም። 

ስለሆነም የእኛ ዋና ዓላማ ሁለተኛው ምርጫ የኦሮሞን ማንነት ወደ አማራነት መቀየር (Assimilate) ማድረግ ይሁን "እንዴት ሆኖ ስራ ላይ ይውላል ለተባለው ጥያቄ የአቶ ተድላ መልስ
1ኛ በስርዓተ ትምህርት በኩል የአማርኛ ቋንቋና የአማራ ባህል ኣንዲስፋፋ ማድረግ።
2ኛ አማርኛ የሚናገሩ ወታደሮችን በኦሮሞዎች ውስጥ ማስፈርና ከኦሮሞዎች ውስጥ የሚመለመሉ ወታደሮችም አማርኛ ብቻ እንዲናገሩ ማድረግ።
3ኛ በኦሮሞ ምድር የሰፈሩ ወታደሮች የኦሮሞ ሴቶችን እንዲያገቡና አማርኛ መናገር እንዲያስተምሩ ማድረግ ሲሆን ከዚህም ጋር ማናቸውም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማለትም የአስተዳደር ፣ የዳኝነት፣ የምጣኔ ሀብት ድርጅቶች ሁሉ የኦሮሞን ማንነትን በማጥፋት ላይ እንዲያተኩሩ ማድረግ፣ ጠቅላይ ግዛቶች ወይም የአስተዳደር ክፍሎችም ለዚህ ማንነት የማጥፋት ዘመቻ በሚያመች መንገድ እንደገና እንዲሸነሸኑ ይደረግ ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሞዎችን ብዛት ለመበረዝ አማራዎችን በተለያዩ የኦሮሞ ክፍሎች ውስጥ  እነሱንም ማስፈር ያስፈልጋል።
.
" ኦሮሞነትን ማጥፋት ዘመቻ በምንም ምክንያት የማይታለፍ (imperative) የመጀመሪያው አጀንዳችን ካልሆነና ማንነታቸውን ይዘው እንዲቆዩ ከተፈቀደ
አማራና ኦሮሞ ወደፊት ሁለት የተለያዩና የሚቀናቀኑ መንግስቶች ሊመሰርቱ ይችላሉ"ካሉ ቦሀላ አቶ ተድላ በመቀጠል "ኦሮሞዎችን ዘመናዊ ትምህርትና የውጪ ቋንቋ ማስተማር የኦሮሞን ብሄረኝነት ስለሚያሳድግ ኦሮሞዎች እንግሊዘኛ ፣ ጣሊያንኛ ወይም ፈረንሳይኛ እንዳይማሩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል"
.
የአቶ ተድላ ኃይሌ ምክር በምን መልኩ ወደ ተግባር ተቀየረ አቶ ተድላ ኃይሌ እንዲህ ይላል "ይህንን የኦሮሞ ማንነት (Assimilate) መለወጥ ደግሞ ንጉሳችን ዳግማዊ ምንሊክ ለእነ ራስ ጎበና፣ ለእነ ፊታውራሪ ኃብተጊዮር ስና ....ለእነ ደጃዝማች ገ/ እግዜብሔር ሞሮዳ ስልጣን በመስጠትና ኦሮሞነታቸውን በመለወጥ አሳይተውናል"
.
ከፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ጋር እንቀጥላለን
"Entrusting the education of the Oromo to the English, the Italian or the French could therefore only end up in nurturing Oromo nationalism."
2005 :page 132-140
.
በአቶ ተድላ ምሁራዊ ምክር :- የተጠናከሩት በዘመኑ የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር የነበሩት የአቶ ሳህሌ ፀዳሉ ደግሞ በ1933 የሚኒስተርነት ስልጣናቸውን ተጠቅመው የሚከተለውን ፀረ- ሰው ልጅ መብት ገፋፊ አዋጅ አወጁ
" ያገር ጉልበት አንድነት ነው አንድነትንም የሚወልደው ቋንቋ ልማድና ሃይማኖት ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ቀዳማዊ መሆኗን ለማስመስከር አንድነቷንም ለማፅናት እስከ አሁን በቆየው ልማዳችን ተማሪ ቤቶቻችንን አስፍተን ቋንቋችንንና ሃይማኖታችንን በመላው በኢትዮጵያ ግዛት በአዋጅ እንዘርጋው ይህ ካልሆነ እስከመቼውም ድረስ አንድነት አይገኝም" 
በመላው በኢትዮጵያ ግዛት ለስጋዊና ለመንፈሳዊ ስራ ያማርኛና የግዕዝ ቋንቋ ብቻ በህግ ፀንተው እንዲኖሩ ሌላው ማናቸውም የአረማውያን ቋንቋ ( የኦሮምኛን ጨምሮ 84 ብሄረሰቦችን ቋንቋ መሆኑ ነው) ሁሉ እንዲደመሰስ ማድረግ ያስፈልጋል" በማለት አቶ ሳህሌ ፀዳሉ በመቀጠል " ሚሲዎኖች ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎችንም ቢሆን እንዳይከፍቱ መከልከል ያስፈልጋል ከከፈቱም የውጭ ቋንቋ መማርም ቢሆን እድሉ ለኢትዮጵያዊያን መሰጠት አለበት"ይላሉ። (ልብ እንበል ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከፈት ትምህርት ቤት ተለይቶ ለኢትዮጵያዊያን መሰጠት አለበት ይላሉ እነዚህ ኢትዮጵያዊያን እነማን ናቸው?)

እንግዲህ ይቺ ናት" ኢትዮጵያዊነት" እየተባለ ቀን ከሌት እንደበቀቀን የሚዘመርላት። 
የአክሊሉ ሀብተወልድን ህልም ለማሳካት እየተንደፋደፈ ያለው አብይ አህመድም በእኛ ትውልድ ፈጽሞ አይሳካለትም።

ኦሮሞነቴን ያላከበረች ኢትዮጵያ ፈጽሞ ህልም ናት።
Gumaa Oromtichaa page.

No comments:

Post a Comment