Friday, May 11, 2012

THE ROLE OF PARLIAMENTS IN SHAPING DEMOCRTIC GOVERNANCE THE ETHIOPIAN CONTEXT FEDERAL AND REGIONAL PERSPECTIVE (የምክር ቤቶች ሚና ዴሞክራሲያዊ መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንፃር)


ለውይይት የቀረበ
አዘጋጅ፤ ሀብታሙ ኒኒ አቢኖ
(LLB, MBA)
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤት ሃላፊ
ማውጫ
ገጽ
የምክር ቤቶች ሚና (The Role of Parliament)……………………………….
3-5
ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር (Democracy & good governance) …….
6-8
ዴሞክራሲያዊ መልካም አስተዳደርና የምክር ቤቶች ሚና (Democratic governance and the role of parliament)…………………………………….

9-10
ማጠቃለያ…………………………………………………………………………..
11

መግቢያ
ይኸ አጭር ጽሑፍ በዋነኛነት ትኩረት የሚሰጠው በየትኛውም የመንግሥት እርከን ላይ የሚገኙ ምክር ቤቶች ዴሞክራሲንና መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ ያላቸውን ሚና ለመቃኘት ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎች ከራሳቸው ምክር ቤት አንፃር ጉዳዩን በመመልከት በውይይት እንዲያዳብሩት በማሰብ ነው፡፡

በሀገራችን እንደማንኛውም የፌዴራል ሥርዓት የሚከተሉ ሀገሮችና የፌዴራሊዝም ባህርይ ሁለት መንግሥታት ሲኖሩ እነዚህም የፌዴራል መንግሥቱ /የክልሎች የጋራ መንግሥት/ እና የክልል መንግሥታት ሲሆኑ ሁለቱም የየራሳቸው የሕግ አውጭነት፣ ሕግ ፈፃሚነትና ህግ ተርጓሚነት ሥልጣን እንዳላቸው በህገ-መንግሥቱ ተደንግጓል፡፡ /በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 51 እና 52/ በጽሑፍ የመንግሥት አካላት ሥልጣን ለመዘርዘር ሳይሆን በዋነኛነት በመንግሥት ሥልጣን ክፍፍል ውስጥ የምክር ቤቶች ሚና ለዴሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር ያለውን አስተዋፅኦ ለመቃኘት ነው፡፡ በተጨማሪም ይኸ ጽሑፍ የመነሻ ሲሆን የበለጠ በውይይት የሚዳብር ይሆናል፡፡


1. የምክር ቤቶች ተግባርና አለም አቀፋዊ ገፅታቸው
በየሀገሩ ሕገ-መንግስት በሚወስነው መሠረት ምክር ቤቶች የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናሉ፡፡
Parliaments carry out their distinctive function within the separation of power. Experts may differ on their precise list of such functions, but there seems broad agreement that at least the following should be included in the tasks undertaken by and expected of all parliaments.
-      Law making.
    -   Approval of taxation and expenditure, generally in the context of the
          national budget.
-      Oversight of executive actions, policy and personnel.
-      Ratification of treaties and monitoring of treaty bodies.
-      Debating issues of national and international moment.
-      Hearing and redressing grievances.
-      Approving constitutional change.

ም/ቤቶች ከላይ የተመለከቱትን ተግባራት እንዲያከናውኑ ምክንያት የሆነው ሕዝብ የመረጣቸው ስለሆኑና ሕዝብን ወክለው እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውኑ     በሕገ-መንግስቱ ሥልጣን ስለተሰጣቸው ነው፡፡
ምክር ቤቶች የሕዝብ ሉዓላዊነት መገለጫዎች ናቸው፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ           ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 8 ይህንን በግልጽ የሚያመላክት ነው፡፡
የሕዝብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጡ መርሆዎች በክልል ሕገ-መንግሥታትም ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ተደንግጓል፡፡

ከላይ በተመለከቱት የምክር ቤት ተግባራት ዋና ዋናዎቹን ስንመለከት
ሀ. ሕግና ፖሊሲን የማውጣት ሥልጣን፣ ሕግና ፖሊሲ ማውጣት ከአንድ ምክር    
   ቤት ተግባራት ውስጥ በመጀመሪያ ረድፍ የሚጠቀስ ነው፡፡ በፌዴራል ደረጃ
   የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕግና ፖሊሲ የማውጣት ስልጣኖች
   በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 በዝርዝር ተሰጥቷል፡፡ ይኸ ም/ቤት ሕግና ፖሊሲን
   የሚያወጣው በሕገ-መንግሥቱ ለፌዴራል መንግሥት በተሰጡት የስልጣን
   ጉዳዮች ላይ ነው በተመሳሳይ ሁኔታ የክልሎችም በሕገ-መንግሥቱ ለክልሎች
   በተሰጡ ጉዳዮች ላይ ሕግና ፖሊሲ የማውጣት ስልጣን አላቸው /አንቀጽ 52/

እነዚህ ም/ቤቶች በሚያወጣቸው ሕጐችና ፖሊሲዎች ይዘትም ሆነ በሂደታቸው    ለዴሞክራሲ ማደግና መጐልበት፣ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ለመልካም አስተዳደር (Good Governance) መስፈን፣ የግልፅነትና ተጠያቂነት መኖር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡

ሕጐቹ በይዘታቸው መብትን የሚያስከብሩና የመንግሥትን ተጠያቂነት የሚያረጋግጡ ከሆኑ ይኸ ሁኔታ ከላይ የገለፅናቸውን የመብት መከበር የግልፅነትና ተጠያቂነት መኖር የመሳሰሉትን መልካም ነገሮች ያጐናጽፋል፡፡ በሌላ ሙልኩ ደግሞ ም/ቤቶች የሚያደርጓቸው ክርክሮችና እነዚህ ክርክሮች የሚመሩባቸው ደንቦች ዲሞክራሲያዊ ሲሆኑ የሚያፀድቋቸው ሕጐችና ፖሊሲዎች የዴሞክራሲ ውጤቶች ይሆናሉ፡፡ የወከላቸው ሕዝብም ከዚህ ብዙ ይጠቀማል ይማራል፡፡

ለ. የክትትልና የቁጥጥር ሥልጣን
በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች አዋጆችን ከማውጣት ባሻገር የህግ አስፈፃሚውን አካል የሚሾሙና የሚሽሩ ናቸው፡፡ ዳኞችም የሚሾሙትና በመጨረሻም የሚሻሩት በምክር ቤቶቹ ነው፡፡  ምክር ቤቶች ህግ አስፈፃሚው ሥራውን በአግባቡና ምክር ቤቱ ባፀደቃቸው ህጐች ምክር ቤቱ ባፀደቀው በጀት እየተፈፀመ መሆኑን በቅርብ የመከታተልና አስፈላጊ የሆኑ ማስተካከያዎች እንዲደረጉ የማዘዝ ስልጣን አላቸው፡፡ ፈፃሚው አካልና ሥራውን በብቃት የማይፈፅም ሆኖ ሲያገኙት የመሻር መብትም ይኖራቸዋል፡፡ ይኸ ለዳኝነት አካሉም የሚሠራ የቁጥጥር ሥርዓት ነው፡፡ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓቱ በምን መልኩ ይከናወናል፡፡




1. Oversight through the committee system
Some tasks, particularly those involving detailed consideration of matter are best performed by smaller group than the House setting in plenary and it is in this respect that committee can play a vital role in exercising oversight of executive action (Parliament and Democracy in the 21st Century page 128).

2.  Oversight by and over non-governmental public agencies
This is done through, Auditor General, Ombudsman for public Administration, Human Right Commission, Anti-Corruption commission in some other countries and office of National Statistics (Statistics to show government policies in a favorable light the independence of a statistics office is best ensured by making it accountable to parliament rather than the government.

3. Oversight through parliamentary questions
In parliamentary system and others where ministers are also members of the legislatures, the parliamentary questioning of ministers on regular basis both orally and writing, forms an important mechanisms of oversight.

4. Parliamentary approval of executive appointments
The process of approval for executive and cabinet appointments, judicial appointments, judicial appointments and a vote of no confidence in Executive and individual ministers.

5. Special commission of enquiry
As a further instrument oversight which parliaments may setup to investigate issues of major public moment. (በኢትዮጵያ  ለጋምቤላ ግጭት፣ በምርጫ 97 የፌዴራል ማግሥት በኦሮሚያ ምክር ቤት ጭምር ይኸ ኮሚቴ ተቋቁሞ የችግሮችን መንስኤ አጣርቷል፡፡)

6. Parliamentary oversight of the security sector
The security sector is a highly complex field, in which parliaments have to oversee such issues like weapon procurements, arm control and readiness/preparedness of military units not all parliamentarians have sufficient knowledge and expertise to deal with these issues in an effective manner.

7. Budgetary Scrutiny and financial control
Parliamentary oversight of government finance can be separated into two broad and spending of revenue ex ante through consideration of its proposal budget; and monitoring of expenditure ex Post, to ensure that it has conformed to the terms which parliament has approved.
And effective monitoring encompasses issues such as the following
-      Has public money been spent on the purposes for which it was assigned?
-      Has it been spent efficiently, and with out west?
-      Has spending been kept with in the budget allocation?
-      Is there evidence of fraud or misappropriation, or other irregularities?
እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው የቁጥጥር ዘዴዎች ዋና አላማቸው የሕዝብና የመንግሥት ሃብትና ንብረት በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን፣ ሥራዎች ሕግና ሥርዓትን መሠረት አድርገው እየተከናወኑ መሆናቸውን ፍትሐዊና ፈጣን ልማት አቅጣጫ መኖሩን፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር (good governance) መስፈኑን፣ የዜጐች መብት፣  ሰላምና ፀጥታ መከበሩን እንደዚሁም በመንግሥት አካላት መካከል የተቀናጀ አሠራር መኖሩን ለማረጋገጥ ምክር ቤቶች የሚጠቀሙባቸው መንገዶች ሲሆኑ አሁን ለያዝነው የምክር ቤቶች ሚና መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንፃር ለሚለው ርዕስ ጠቃሚ መሣሪያዎች ናቸው፡፡

2. ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር (Democracy and good governance)
በአንድ ሀገር ውስጥ መልካም አስተዳደር እንዲኖር የዴሞክራሲ ሥርዓት መኖር ይገባዋል፡፡ ይሁንና ዴሞክራሲ ሥርዓት ባለበት ሁሉ መልካም አስተዳደር ይኖራል ማለት አይደለም፡፡ የዴሞክራሲ ሥርዓት ባለበት አገር ሁሉ ቀልጣፋ የመንግሥት አሠራር ይኖራል ማለት አይደለም ዴሞክራሲ ባለበት ሁሉ ህዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበት ፈጣን ልማት ይኖራል ማለት አይደለም፡፡

ቀልጣፋ የመንግሥት አሠራር፣ ከሙስና የፀዳ ሙስና በቁጥጥር ስር የገባበት ለፈጣን እድገት የተመቻቸ ሁኔታን የሚፈጥር መንግሥት ባለበት ብቻ ነው መልካም አስተዳደር ሊኖር የሚችለው፡፡

አሁን በያዝነው ርዕስ የም/ቤቶቹን ሚና ለዴሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር ለማየት መልካም አስተዳደር ይዘቶች ምንድናቸው? (What are components of good governance?) የሚለውን ማየት ተገቢ ነው፡፡ እነዚህም

  1. Capacity of the state:- to function in service of the public good this requires a trained professional civil service.
  2. Commitment to the public good:- this must be reinforced by institutions that reward public spirited behavior and punish betrayals of the public trust.
  3.  Transparency and accountability:- the business and conduct of the state must be open and responsible to the scrutiny of other state actors and of the public. State power must be accountable before other countervailing, monitoring institution in the state and civil society.
  4. Rule of law:- Governance can only be good and effective when it is restrained by the law and when there are professional independent authorities to enforce the law in a neutral, predictable fashion. Effective government, well functioning market, and the protection of human rights all require that there be clear rules about what constitutes acceptable conduct in all realms of economic social and political life. All actors, public and private must have confidence that the rules will be observed and enforced.

  1. Participation and Dialogue:- Through institutionalized channels that enable the public to provide input to the policy process, to correct mistakes in policy design and implementation, and to promote social inclusion institutionalized participation, as through public hearing by legislative committee and regulatory agencies, also provides channels for setting (or at least narrowing ) conflict over interest and values and for making broadly legitimate policy choices policies will be more likely to be stable and sustainable when they enjoy popular understanding and support.

  1. Social Capital:- In the form of network and association that draw people together in relation of trust, reciprocity, and voluntary cooperation for commends. Social capital fosters investment and commerce and breeds the civic sprit, participation, and respect for that are crucial foundation and good governance. 

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው የመልካም አስተዳደር መገለጫዎችን የምክር ቤት ሚና ናቸው ብለን ከጠቀስናቸው ዋና ዋና ተግባራት በተለይም ሕግና ፖሊሲ የማውጣት እንዲሁም በሌሎች የመንግሥት አካላት የሚደረገው የክትትልና የቁጥጥር ተግባር በዋነኛነት መልካም አስተዳደርን በተለይም የግልጽነትና የተጠያቂነት መርሆን ከማስፈን አንፃር ምክር ቤቶች የላቀ ሚና እንዳላቸው ያሳየናል፡፡ ይኸም በሁለት መንገድ ሊከናወን ይችላል፡፡ በተለያዩ አዋጆችና ፖሊሲዎች በመልካም አስተዳደርና ለዴሞክራሲያዊ ሂደት መጐልበት ምቹ ሁኔታን መፍጠር ሲሆን ሁለተኛው የወጡ አዋጆችንና ፖሊሲዎችን መሠረት ባደረገ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ በሚወሰዱ እርምጃዎች ምክር ቤቶች ለዴሞክራሲያዊ መልካም አስተዳደር መስፈን ዋነኛውን ቁልፍ ተግባር ይከናወናሉ፡፡



3. ዴሞክራሲያዊ መልካም አስተዳደርና (Democratic governance)
    የምክር ቤቶች ሚና
ምክር ቤቶች ከላይ የገለፅናቸውን ተግባራት በአግባቡ የሚያከናውን ከሆነ ለሀገራችን ዕድገትና ብልፅግና፣ ለዜጐች መብት መከበር፣ ለዲሞክራሲና ለህግ የበላይነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡

በእርግጥ ተግባራቱን በአግባቡ መወጣት አለባቸው ውስጣዊ አሠራራቸው ዴሞክራሲያዊነትን የተከተሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህም የሚከተሉትን የዴሞክራሲያዊ ም/ቤት ባህርይ መከተል ይኖርባቸዋል፡፡

A framework for a democratic parliament
Representative:- that is socially and politically representative of diversity of the people, and ensuring equal opportunities and protections for all its members.
Transparent:- that is being open to the nation through different media and transparent in the conduct of its business
Accessible: - this means involving the public, including the associations and movement of civil society, in the work of parliament
Accountable: - This involves members of parliament being accountable to electorate for their performance in office and integrity of conduct.
Effective: - this means the effective organization of business in accordance with these democratic values, and the performance of parliament’s legislative and oversight function in manner that serves the needs of the whole population.

N.B:- One of the dimensions of democracy consists in the institution of representative and accountable government, which together determine the laws and policies for society and secure respect for the rule of law with in the traditional separation of powers between the executive, legislature and judiciary parliament as the freely elected body holds a central place in any democracy. It is the institution through which the will of the people is expressed and through which popular self government is realized in practice. 
As agent of the people, parliaments represent them in dealings with the other branches of government and with various international and sub-national bodies.

How well they fulfill this mediating role, and how representative of the people they are in all their diversity is an important consideration for a democratic parliament.


4. ማጠቃለያ
ህገ-መንግሥታችን ሉአላዊነት ሲባል የህዝብ ሉአላዊነት ማለት እንደሆነ፣ ይኸ የህዝብ ሉአላዊነት ከሚገለፅባቸው መሠረታዊ መስኮች አንዱና ዋነኛው ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊ አኳኋን በሚመርጣቸው ተወካዮች አማካኝት እንደሆነ በግልጽ ያስቀምጣል ከዚህ በመነሳት በየደረጃው በህዝብ ዲሞክራሲዊ ምርጫ ስለሚቋቋሙት ምክር ቤቶች ሥልጣንና ሃላፊነትም ይደነግጋል፡፡ ምክር ቤቶቹ የህዝቡ ሉአላዊነት መገለጫ የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር (Democratic Governance) እምብርትና የዲሞክራሲያዊ አገዛዝ አውራ ተቋሞች ናቸው፡፡ ሌሎቹ የዲሞክራሲያዊ አገዛዝ ተቋሞችና ድርጅቶች የሚመሰረቱት በምክር ቤቶቹና ምክር ቤቶቹ በሚሰሯቸው ስራዎች ላይ ነው፡፡ በመሆኑም የእነዚህ ምክር ቤቶች መጠናከር ለዲሞክራሲያዊ አስተዳደር መስፈን ወሳኝ ናቸው፡፡












ዋቢ መፃህፍት
  1. Parliament and democracy in the Twenty-First century a guide to good practice (2006) IPU

  1. The parliamentary mandate (2000) IPU

  1. Evaluating parliament a self assessment toolkit for parliament (2008) IPU

  1. በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጉዳዮች (ግንቦት 1994)

  1. ጌታቸው አሰፋ የፌዴሬሽን ም/ቤት ልዩ ባህርያትና የምክር ቤቶች ሚና በአለም የዴሞክራሲ ቀን ለውይይት የቀረበ

No comments:

Post a Comment